Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
Channel ✓ Telegram verified @fdre_molsofficial
FDRE, Ministry of Labor and Skills
Rating out of 10 5.9 Rating out of 10 5.9 /10 System score · How ratings work
- Subscribers
- 70,670
- Last post
- 16d ago
Collected on 2026-11-21 · not real-time
Introduction
FDRE, Ministry of Labor and Skills
Show the original Telegram description
FDRE, Ministry of Labor and Skills
Rating breakdown
Algorithm v1 · How ratings workSystem score 5.9 (1 + contributions 4.90) · final 5.9
Dimension Input Value Weight Contribution
Content quality Not reviewed yet (counted as neutral 0.5) · 40% 0.50 40% +1.80
Safety Not reviewed yet (counted as neutral 0.5) · 30% 0.50 30% +1.35
Audience 70,670 subscribers · 12% 0.70 12% +0.76
Recent activity Last post 16d ago · 10% 0.70 10% +0.63
Telegram verified Has verified badge · 4% 1.00 4% +0.36
Official backlink No linked tools · 4% 0.00 4% —
Recent posts
View all on Telegram"የሥራ ማዕከላት ግንባታ በጥራትና በፍጥነት ተገንብተው ለታለመላቸው ዓላማ መዋል ይገባቸዋል።" ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ
የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙትን ዘመናዊ የሥራ ማዕከላት የግንባታ ሂደትና ያሉበትን የአፈጻጸም ደረጃ የመስክ ምልከታ አካሂደዋል።
በመስክ ምልከታው ወቅት እንደተገለጸው፤ የተጀመሩት የሥራ ማዕከላት ግንባታ በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በፍጥነትና በጥራት ተጠናቀው ለታለመላቸው የልማትና የወጣቶች አገልግሎት ዓላማ መዋል እንደሚገባቸዉ ተመላክቷል።
የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ እንደገለጹት እየተገነቡ ያሉ የሥራ ማዕከላት ለወጣቶችና ለሥራ ፈላጊዎች በአንድ ማዕከል (One-Stop Service) ፈጣንና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የግንባታው ጥራትና ደረጃ ሳይጓደል በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተጠናቆ ለታለመለት ዓላማ መዋል ይገባቸዋል።
ግንባታውን እያከናወኑ የሚገኙ የሥራ ተቋራጮች በበኩላቸዉ የግንባታውን…
15.5K views
ሥልጠናን ከኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር ብቁና ምርታማ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተሰራ ነው፡፡
ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓቱን ከሥራ ገበያውና ከኢንዱስትሪው ተጨባጭ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር ብቁ፣ ምርታማና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተሠራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትር ዴኤታው ይህን የገለጹት የSTEP IV – Horti-Skills የሆርቲካልቸር ክህሎት ልማት ፕሮጀክት ማስጀመሪያና የትግበራ ዕቅድ ዝግጅት መድረክ ላይ ነው።
የክህሎት ልማት ስኬት የሚለካው በሚሰለጥኑ ዜጎች ቁጥር ብቻ ሳይሆን፣ ሠልጣኞች በሥራ ገበያው በሚኖራቸው ተሳትፎ፣ በሚያገኙት የሥራ ዕድል፣ በሚፈጥሩት የራስ ሥራና ለኢኮኖሚው በሚያበረክቱት አስተዋጽኦ መሆኑን አስረድተዋል።
ፕሮጀክቱ በሥልጠና ተቋማትና በሆርቲካልቸር ኢንዱስትሪው መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር፣ የክህሎት ክፍተቶችን በመሙላትና የአሰልጣኞችን ብቃት በማሳደግ የዘርፉን የ…
15.7K views
በ22 ቀናት ንቅናቄ ከ25 ሺህ በላይ የሥራ ዕድሎች ተፈጠሩ
የአዲስ አበባ ከተማ ሠራተኛና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የሁለተኛው ዙር የ22 ቀናት የሥራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄ ዕቅድ አፈጻጸምን ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች ጋር ገምግሟል።
በግምገማው በንቅናቄው ወቅት 25,944 የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸው፣ ከ406.6 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መመቻቸቱና 746 ኢንተርፕራይዞች መደራጀታቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም 29,409 ሥራ ፈላጊዎች በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከ56 ሺህ በላይ ዜጎች በለስላሳና ቴክኒክ ክህሎት ሥልጠናዎች ተሳትፈዋል።
የግምገማ መድረኩን የመሩት የቢሮው የሥራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሰ፣ ከመጀመሪያው ዙር ንቅናቄ የተገኙ ልምዶችንና የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ የተቀናጀና ውጤትን ያማከለ አፈጻጸም ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሁሉም ክፍለ ከተሞች በአንድ ዕቅድና የሪፖርት ሥርዓት በመመራት፣ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እንዲሠሩም አቅጣጫ ሰ…
15.3K views
መሥሪያ ቦታ አቅርቦትን ማሳደግና አስተዳደሩን ማጠናከር ለሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ነው
የመሥሪያ ቦታ አቅርቦትና አስተዳደርን ማሻሻል የኢንተርፕራይዞችን ዘላቂ ዕድገት ከማረጋገጥ ባለፈ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠርና የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
ለዚህም የመሥሪያ ቦታዎችን በበቂ መጠን ከማቅረብ ባሻገር በፍትሐዊነትና በግልጽ የአስተዳደር ሥርዓት መምራት ይጠይቃል።
በጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፖሊሲ ውስጥ የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት ለኢንተርፕራይዞች ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንደ ወሳኝ ግብዓት ተቀምጧል።
በዚህ መሠረት በ2019 በጀት ዓመት 11,487 ሼዶችን በመገንባት፣ ሼድ ለሚፈልጉና ለማይፈልጉ የሥራ መስኮች 126,300 ሄክታር የለማ መሬት በማዘጋጀት 49,500 ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢንተርፕራይዞች አቅም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ መላኩ ወልደዮሐንስ እንዳብራሩት፣ የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት ለኢንተርፕራይዞች የሥራ መጀመሪያ መሠረት ብቻ ሳይ…
14.6K views
በክልሉ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ጋር በመተባበር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፣ ሥራና ክህሎት ቢሮ፣ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎችን በጋራ ገመገመ፡፡
በመድረኩ ላይ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም ሸንገል በክልሉ የሚገኙ ኮሌጆች የሚሰጡት የትምህርትና ስልጠና ስራዎች ከተቋሙ ጋር በቅንጅት የሚተገበር በመሆኑ በእያንዳንዱ አፈጻጸም ላይ ተናቦና ተባብሮ መስራት እንደሚጠበቅ አብራርተዋል።
በዚህም ረገድ የተቋማቱን እቅድና አፈጻጸም በጋራ መገምገም እና እንደአስፈላጊነቱ ተደጋግፎ ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
አክለውም የአሶሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች የሚደነቁና ለሌሎች ተቋማት ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥሩ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ እቅዶችን መከለስና ከሌሎች አቻ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር አብሮ መለወጥ ላይ ማተኮር እንደሚገ…
12.5K views
Similar Telegram resources
Profile
Type Channel
Username t.me/fdre_molsofficial
Category News
Telegram verified Yes
Collected 2026-11-21
About the data
Counts, verification and recent posts come from periodic snapshots of Telegram's public pages and are not real-time. Descriptions are edited; the original text is available under the original description.